በማካካሻ የሚፈጸም ወሲብ ሲባል ግብረስጋ ሲፈጽሙና በምትኩ አንድ ነገር ሲያገኙ ነው። ለምሳሌ፡ ወሲብ ሲባል እንደሚከተለው ነው፥
- – በወብ ካሜራ ውስጥ ትታያለህ
- – አንድ ሰው ማስቱርበይት (ወይም ግብረ ኣናን) ሲፈጽም ትመለከታለህ
- – በሌላው ሰው ፊት ግብረ ኣናን ትፈጽማለህ
- – ከሰው ጋር በግብረ ሥጋ ትገናኛለህ ወይም የግብረ ሥጋ ነክ ተግባሮች ትፈጽማለህ
ማካካሻው ለምሳሌ ገንዘብ፡ የመኝታ ቤት፡ ማጓጓዣ፡ ስማርትፎን፡ ልብሶች፡ ሲጋራ፡ ኣልኮል ወይም ኣደንዛዥ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።
ኣንድ ሰው ማካካሻ ለማግኘት ሲል ወሲብ የሚፈጽምበት ምክንያቶች ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ገንዘብ ለማግኘት ሊሆን ይችላል። ወይም ተግድዶ ወይም ተታልሎ ሊሆን ይችላል። ወይም ድርጊቱ ደስ የሚያሰኝና የማንነትን ጉድለት የሚያሟላ ሊሆን ይችላል።
በስዊድን ኣገር ኣስከፍሎ የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ክልክል ኣይደለም። ከፍሎ ወሲብ ማግኘት ግን ክልክል ነው።
ጥበቃና ድጋፍ የማግኘት መብት አለህ
ያለህበትን ሁኔታ ለመለወጥ ድጋፍ ትፈልጋለህ ወይ? የምታነጋግረው ሰው እንዲኖርህ ትፈልጋለህ ወይ? ሁኔታው ለነዚያ በማካካሻ መንገድ ግብረ-ስጋ የሚፈጽሙት የተለየ ሁኖ ሊታይ ይችላል። ኣንዳንዶቹ ደስ ይላቸዋል፡ ሌሎቹ ደግማ በጣም ያሰቃያቸዋል ችግርም ይፈጥርባቸዋል። ይሁንና ጥሩ ስሜት ይኑርህ ኣይኑርህ፡ ለራስህና ለሁኔታህ የሚመች ድጋፍ ለማግነኘት መብት ኣለህ።
ለዓመጽ የተጋለጥክ ከሆንክ መረጃ፡ ጥበቃና ድጋፍ የማግኘት መብት ኣለህ። የምታነጋግረው ሰውም ልታገኝ ትችላለህ። ልጆች ካሉህ፡ ልጆቹም የድጋፍ መብት ኣላቸው።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ድርጅቶች እንዲረዱህ መጠየቅ ትችላለህ
የምትኖርበት ኮሙን
በማንኛውም ግዜ ከምትገኝበትን ኮሙን ግንኙነት ማድረግ ትችላለህ። እንዲሁም የጤና ማእከልና የወጣቶች ክሊኒክ ወይም ፖሊስን ኣነጋግራቸው።
ፖሊስ
ተለፎን 114 14. ጉዳዩ ኣስቸኳይ ከሆነ
ሁልግዜ በ 112 ደውል
www.polisen.se
BRIS 116 110
የድጋፍ ተለፎን ለወጣቶች። ለማውራት ወይ ቻት ማድረግና ኢመይል ማድረግ ትችላለህ። ማንነትህን ላለመግለጽ ይቻላል።
www.bris.se
1000 Möjligheter – ኣንድ ሺ ኣማራጮች
ወጣቶች ስለ ሁኔታቸው የሚያወሩበት የድጋፍ ቻት።
http://1000mojligheter.se/
Rädda barnen 0200-77 88 20
ለወጣቶችና በስዊደን ኣገር ገና የገቡ የሚመለከት የድጋፍ ተለፎን። ማንነትህን ላለመግለጽ ትችላለህ። መልስ የሚሰጡህ ሰዎች ብዙ ቋንቋዎች ይናገራሉ።
www.rb.se/helpline
Mikamottagningen Göteborg 020-32 73 28
ጥሪ፡ ድጋፍና ተግባራዊ እርዳታ የሚሰጥህ ኣመራር። በወሲብ ምትክ ማካካሻ ያገኙ ወይም የተጎዱ ሰዎች ሚካሞታግኒንገንን ሊያነጋግሩ ይችላሉ። ማንነትህን ላለመግለጽ ይቻላል።
mikamottagningen@socialresurs.goteborg.se
Mikamottagningen Stockholm 08-508 25 501
ጥሪ፡ ድጋፍና ተግባራዊ እርዳታ የሚሰጥህ ኣመራር። በወሲብ ምትክ ማካካሻ ያገኙ ወይም የተጎዱ ሰዎች ሚካሞታግኒንገንን ሊያነጋግሩ ይችላሉ። ማንነትህን ላለመግለጽ ይቻላል።
http://www.stockholm.se/mikamottagningen
KST Malmö 020-35 40 40
ጥሪ፡ ድጋፍና ተግባራዊ እርዳታ የሚሰጥህ ኣመራር። በወሲብ ምትክ ማካካሻ ያገኙ ወይም የተጎዱ ሰዎች KSTን ሊያነጋግሩ ይችላሉ። ማንነትህን ላለመግለጽ ይቻላል።
kst@malmo.se
NMT – በየሴተኛ አዳሪነት እና በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የሚደረገውን ብሄራዊ ዘዴ 020-390 000
NMT ለእርዳታና ድጋፍ ትክክለኛ ሰው ታገኝ ዘንድ ይተባበራል።
www.nmtsverige.se
Plattformen Civila Sverige mot människohandel – በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የሚታግለ የስዊድን ሲቪላዊ መድረክ
ላንተው ለዓመጽ የተጋለጥከውን የሚረዳ ድርጅት። በኤመይል ኣነጋግራቸው፥
info@manniskohandel.se
የድህነት ሰራዊት Frälsningsarmén 08-562 282 00
ትልቅ ማሕበራዊ ስራ ያላት ቤተ-ክርስትያን። በምትኖርበት ከተማ ከሚገኙትን ሳልቨሽን ኣርሚ ሂደህ ኣነጋግራቸው ወይም እርዳታ ለመማግኘት ደውልላቸው ወይም ኢመይል ላክላቸው።
manniskohandel@fralsningsarmen.se